Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል ትራንስፎርመሮችን ሲዘርፉ እጅ ከፍንጅ የተያዙ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ቀርሳ ማሊማ ወረዳ ሌመን ከተማ አዋሽ አቡ ጉቱ አካባቢ እና በሰበታ አዋስ ወረዳ አለምገና ከተማ አካባቢ ትራንስፎርመር ሲሰርቁ እጅ ከፍንጅ የተያዙ ሦስት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

የኦሮሚያ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት እንዳስታወቀው÷ ትራንስፎርመሮቹ ለመጠጥ ውሃ አገልግሎት የሚሰጡ ባለ 50 ኬ.ቪ.ኤ እና ባለ 100ኬ.ቪ.ኤ ናቸው፡፡

በተመሳሳይ በቡራዩ ከተማ አስተዳደር ታጠቅ አካባቢ ለኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎት የሚሰጡ 3 ባለ 50 ኬ.ቪ.ኤ ትራንስፎርመሮች ላይ የስርቆት ወንጀል ሙከራ ሲደረግ ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ ንብረቱን ማዳን መቻሉን የኤሌክትሪክ አገልግሎት መረጃ ያመላክታል፡፡

ከ2014 ዓ.ም አጋማሽ ጀምሮ በሰበታ፣ በአለምገና፣ በቢሾፍቱ፣ በሌማን፣ በገላን እና በቡራዩ ከተሞችና አካባቢዎች ከ18 በላይ ትራንስፎርመሮች እና ከ400 ሺህ ሜትር በላይ የኤሌክትሪክ ሽቦ የስርቆት ወንጀል መፈጸሙ ተጠቁሟል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.