Fana: At a Speed of Life!

የወባ በሽታን ለመከላከል የሚውል 45 ሚሊየን ብር ግምት ያለው የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግስት የወባ በሽታን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ለሚያደረገው ጥረት የሚውል 45 ሚሊየን ብር ግምት ያለው የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ፡፡

ድጋፉም÷ 550 ማይክሮስኮፕ እና ሌሎች የቤተ ሙከራ መመርመሪያ ቁሳቁስን ያካተተ ነው፡፡

ድጋፉን ያደረጉት የአሜሪካ ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት እና አይካፕ ኢትዮጵያ መሆናቸውን የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

ድጋፍም የወባ በሽታን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ለሚደረገው ጥረት በስድስት ክልሎች በሚገኙ የጤና ተቋማት አገልግሎት ላይ እንደሚውሉ ተገልጿል፡፡

የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ ድጋፉን በተረከቡበት ወቅት እንደገለጹት÷ በጤናው ዘርፍ የወባ በሽታን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠር እና ለማስወገድ በሚደረገው ጥረት መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ድጋፍ ውጤታማ ነው፡፡

የአሜሪካ ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት ዳይሬክተር ቲሞቲ ስቲን በበኩላቸው÷ የወባ በሽታን በመዋጋት ረገድ ያለን አጋርነት ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

የአይካፕ ዳይሬክተር ዶ/ር ዘነበ መላኩ ድጋፉን በማድረጋቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል፡፡

ከድጋፉ መካከል የተወሰኑት በግጭት ለተጎዱ የጤና ተቋማት እንደሚላኩም ተጠቁሟል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.