Fana: At a Speed of Life!

የኬንያው ንግድ ባንክ በኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፍ ለመሠማራት ያለውን ፍላጎት ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኬንያ ንግድ ባንክ ኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፏን ለውጭ ባለሀብቶች ክፍት ለማድረግ መወሰኗን ተከትሎ በሀገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ ለመሰማራት ፍላጎት እንዳለው ገለጸ፡፡

የባንኩ ከፍተኛ የሥራ ኃለፊዎች ልዑክ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽንን ጎብኝቷል፡፡

ልዑኩ እንደገለጸው፥ በቅርቡ የኢትዮጵያ መንግስት የፋይናንስ ዘርፉን ለውጭ ባለሀብቶች ክፍት ለማድረግ መወሰኑን አድንቋል፡፡

ይህን ተከትሎም የኬንያው ንግድ ባንክ በኢትዮጵያ በፋይናንስ ዘርፍ ለመሳተፍ ፍላጎት አለው ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ምክትል ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁን፥ የኢንቨስትመንት ፖሊሲዎች፣ በቅርብ የተደረጉ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች እንዲሁም የፋይናንስ ዘርፉ ለውጭ ባለሀብቶች ክፍት የሚሆንበትን ዓላማ ለልዑካን ቡድኑ አስረድተዋል፡፡

የኬንያ ንግድ ባንክ ከ125 ዓመታት በላይ በባንክ ዘርፍ ልምድ ያለው እና በሰባት የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት በመስራት ላይ እንደሚገኝ የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.