Fana: At a Speed of Life!

ኤሎን መስክ የትዊተር ግዢያቸውን አጠናቀቁ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኤሎን መስክ ትዊተር የተሰኘውን የማህበራዊ ትስስር ገጽ በ44 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር የመግዛት ሂደትን አጠናቀቁ።
 
በዓለም ቁጥር አንድ ባለሃብት የሆኑት ኤለን መስክ የትዊተር ግዢ ሒደትን ማጠናቀቃቸውን ተከትሎ የኩባንያውን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችን ከስራ አሰናብተዋል።
 
ኤሎን መስክ ጉዳዩን አስመልክተው በማህበራዊ ትስስር ገጻቸውባሰፈሩት ጽሑፍም “ወፏ ነጻ ወጣች“ በማለት ትዊተርን የግላቸው እንዳደረጉ ጠቁመዋል፡፡
 
ይሁን እንጂ ኩባንያው የግዢ ሂደቱ መጠናቀቁን አስመልክቶ እስካሁንያለው ነገር አለመኖሩ ተመላክቷል፡፡
 
ምንጭ፦ ቢቢሲ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.