Fana: At a Speed of Life!

ዓለማችን ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ ከፍተኛ ተግዳሮቶች ተጋርጠውባታል – ፕሬዚዳንት ፑቲን

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለማችን ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ የማይገመቱ እና አደገኛ ችግሮች ተጋርጠውባታል ሲሉ የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን ገለጹ፡፡

ፕሬዚዳንት ፑቲን ሞስኮ በሚካሄደው የቫልዳይ ዓመታዊ ስብሰባ ላይ ባደረጉት ንግግር ÷ አሁን ላይ የምዕራባውያን የበላይነት ዘመን ባልተጠበቀ ሁኔታ እያበቃለት ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ዓለም አሁን ላይ “ታሪካዊ ድንበር ላይ ቆማለች” ያሉት ፕሬዚዳንቱ ÷ መጪው ጊዜ ምናልባትም በጣም አደገኛ እና ሊገመት የማይችል እንደሚሆን ጠቁመዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ፑቲን ምዕራባውያን አደገኛ፣ ደም አፋሳሽ እና አስቀያሚ የጂኦ ፖለቲካ ጨዋታ በመጫወት ላይ መሆናቸውንም አስረድተዋል፡፡

በተለይም አሜሪካ እና የሰሜን ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) አጋሮቿ የሩሲያ-ዩክሬን ግጭት እንዲቀሰቀስ እና በታይዋን ውስጥ በቻይና ሉዓላዊነት ላይ ቀውስ በመፍጠር ዓለም አቀፍ የበላይነትን ለማስጠበቅ እንደተባበሩ አንስተዋል፡፡

ሁልጊዜም በማስተዋል አምናለሁ ያሉት ፕሬዚዳንት ፑቲን÷ አዲሱ ሁሉን አቀፍ ዓለም እና የምዕራቡ ዓለም ስለጋራ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ውይይት እንደሚያደርጉ እምነቴ ነው ብለዋል።

ፕሬዚዳንት ፑቲን ውይይቱ አካታች በሆነ መልኩ በፍጥነት ቢካሄድ የተሻለ ይሆናል ማለታቸውን አር ቲ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.