Fana: At a Speed of Life!

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ለተቋሙና አካባቢው ነዋሪ የሚሆን የእጅ ማጽጃ ሳኒታይዘር ማምረት ጀመረ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል የእጅ ማጽጃ ሳኒታይዘር ማምረት መጀመሩን  የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ  አስታወቀ።

በዩኒቨርሲቲው ጤና ሳይንስና ህክምና ኮሌጅ የፋርማሲ ትምህርት ክፍል ኃላፊ እንዲሁም የኦቶና መማርያና ህክምና ሆስፒታል የፋርማሲ ክፍል ኃላፊ መምህር ታምራት ባልቻ የኮሮና ቫይረስ ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ መሆኑን ተከትሎ ወረርሽኙን ለመግታት ተቋሙ የበኩሉን ሀላፊነት እንዲወጣ ስራዎች እየተከናወነ መሆናቸውን ገልፀዋል።

በአገር ደረጃ የእጅ ማጽጃ ሳኒታይዘር ዕጥረት መኑሩን ታሳቢ በማድረግም ወደ ምርት ሂደት መገባቱን የተናገሩት መምህር ታምራት፥ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል አገልግሎት ላይ እንዲውል የተዘጋጀው ሳኒታይዘር የኬሚካል ውዕደትን በተመለከተ ኢታኖል 80.000%፣ ሃይድሮጂን ፔር ኦክሳይድ  0 ነጥብ 125% እንዲሁም ግላይሴሮል  1 ነጥብ 421% በጥቅም ላይ መዋሉን አስታዉቀዋል።

እጅን ለማጽዳት የሚጠቅመው ይህ ሳኒታይዘር የኮሮና ቫይረስን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ጉልህ ሚና እንደሚኖረው እና ለጊዜው የተመረተው ሳኒታይዘር ኮሮናን ለመከላከል በዞን ደረጃ ለተቋቋመው ግብረኃይልና ለጤና ባለሙያዎች አገልግሎት እንደሚውልም ጠቁመዋል።

ምርቱን በብዛት በማምረት ለሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ተደራሽ ለማድረግ ጥረት እንደሚያደርጉና ለዚሁም የዩኒቨርስቲው አስተዳደር ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

 

በኢብራሂም ባዲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.