Fana: At a Speed of Life!

የደም ማነስ መንስኤ እና ምልክቶች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የደም ማነስ በቂ ቀይ የደም ሴል ሳይኖር ሲቀር የሚከሰት የጤና እክል ነው።

የደም ማነስ የሚባለውም የሂሞግሎቢን መጠን ለወንዶች ከ13 ነጥብ 5 ግራም/ደሊ በታች እንዲሁም ለሴቶች ደግሞ ከ12 ግራም/ደሊ በታች ሆኖ ሲገኝ ነው::

የደም ማነስ መንስኤዎች የተመጣጠነ ምግብ እጥረት፣ የአንጀት መታወክ፣ ሥር በሰደዱ በሽታዎች፣ ኢንፌክሽን እና ሌሎች ሁኔታዎች መሆናቸው ይነገራል፡፡

እንዲሁም በወር አበባ ላይ ያሉ ሴቶች፣ ነፍሰጡሮች እና ሥር የሰደደ የጤና እክል ያለባቸው ሰዎች ለዚህ ችግር የተጋለጡ መሆናቸውን ከጥቁር አንበሳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ገፅ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል፡፡

ከደም ማነስ ምልክቶች ውስጥ የድካም ስሜት ፣ራስ ምታት ፣ የትንፋሽ ማጠር፣ የቆዳ መገርጣት እና መድረቅ፣ የልብ ምት መጨመር ፣ በታችኛው እግር ላይ ያልታሰበ እንቅስቃሴ፣ የእጅ እና እግር መቀዝቀዝ፣ በአንዱ ወይም በሁለቱም ጆሮዎች ላይ ያልተለመደ ድምጽ ወይም ጩኸት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

የደም ማነስ ካለብዎም የአይረን መጠናቸው ከፍተኛ የሆኑ ምግቦችን እንደ የበሬ ሥጋ፣ አረንጓዴ ቅጠላማ አትክልቶች፣ ለውዝ፣ የወተት ተዋጽኦዎች፣ የፎሊክ አሲድ ይዘታቸው ከፍተኛ የሆኑ ምግቦች እንደ ሎሚ እና ብርቱካን፣ እና ጥራጥሬዎች መመገብ ይመከራል::

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.