Fana: At a Speed of Life!

ለአፍሪካ ችግሮች እልባት ለመስጠት የወጣቶችን አቅም መጠቀም ያስፈልጋል- አቶ አደም ፋራህ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ለአፍሪካ ችግሮች እልባት ለመስጠት የወጣቶችን አቅም በከፍተኛ ሁኔታ መጠቀም እንደሚገባ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ ገለጹ፡፡

ብልጽግና ፓርቲ ከመላው አፍሪካ ለተወጣጡ የአፍሪካ ወጣት መሪዎች ጉባዔ ተሳታፊ ለሆኑ እንግዶች የእንኳን ደህና መጣችሁ መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት አካሂዷል፡፡

በመርሐ ግብሩ ላይ አቶ አደም ፋራህን ጨምሮ የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ አባላት መታደማቸው ተገልጿል፡፡

በመድረኩ አፍሪካዊ ወንድማማችነትን  የሚያጠናክሩ ሐሳቦች መንጸባረቃቸውን ከፓርቲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

አቶ አደም ፋራህ በመርሐ ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄዎችን መፈለግ እንደሚገባ አንስተዋል፡፡

በተለይም የወጣቶችን አቅም በመጠቀም በፈጠራ የዳበረች አህጉርን ለመገንባት ዛሬ ነገ ሳንል መነሳት አለብን ነው ያሉት፡፡

ለሁለንተናዊ ብልጽግና ከፍተኛ አቅም የሚፈጥረው የተቋም ግንባታ ላይ ሀገራት ሊሰሩ እንደሚገባ ጠቅሰው÷ ኢትዮጵያም በዚህ ረገድ ሰፊ እንቅስቃሴ እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል፡፡

አፍሪካውያን በህብረት ሲቆሙ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ተሰሚነታቸው እንደሚጨምር እና በዚህ ረገድ ሰፊ እንቅስቃሴ በአፍሪካ ሀገራት መካከል መደረግ እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.