Fana: At a Speed of Life!

“ቡድኑ ትጥቅ ፈትቶ ፖለቲካዊ ኅልውናው ማክተም አለበት” – አብን

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)በኢትዮጵያ መንግስትና በአሸባሪው ህውሓት መካከል በሚካሄደው የሠላም ንግግር ቡድኑ ትጥቅ እንዲፈታ እና ፖለቲካዊ ኅልውናው እንዲያከትም መደረግ አለበት ሲል የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ “አብን” ገለጸ፡፡

“አብን” በኢትዮጵያ መንግስትና በአሸባሪው ህወሓት መካከል በደቡብ አፍሪካ እየተካሄደ ስላለው የሠላም ውይይት ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥቷል።

እራሱን የትግራይ ነፃ አውጪ ብሎ የሚጠራው ትህነግ ከምሥረታው ጀምሮ የአማራን ሕዝብ ሲያዳክም እና ኢትዮጵያን ሲበዘብዝ እንደቆየም በመግለጫው ተነስቷል፡፡

መግለጫው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጥቃት እንዳይደርስበት ሲጠብቅ የነበረው መከላከያ ሠራዊት ላይ ጥቃት መፈጸሙንም አስታውሷል፡፡

አሸባሪው ትህነግ በሦስት ዙሮች በተለይ በአማራና አፋር ክልሎች በፈጸመው ወረራ ንጹሀንን ጨፍጭፏል በንብረት ላይም ከፍተኛ ውድመት አድርሷል፡፡

“አብን” ÷ የትህነግ ቡድን በባሕሪው በሰላማዊ አማራጮች የማያምን እንደሆነም አስታውሷል፡፡

ከቡድኑ ጋር የሚደረገው ውይይት ከቀጠለም ግን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ትጥቅ አንዲፈታ እና ፖለቲካዊ ኅልውና እንዲያከትም መደረግ ይኖርበታልም ብሏል መግለጫው፡፡

የአማራ ህዝብ የሚያነሳቸውን የራያና የወልቃይት የማንነት ጥያቄዎችን ውይይቱ ግምት ውስጥ ማስገባት እንዳለበትም መግለጫው ጠቁሟል፡፡

በቡድኑ የተጨፈጨፉ ንጹሐንና የወደሙ መሠረተ ልማቶችም በልካቸው መነሳት እንዳለባቸው ተነስቷል፡፡

በመሆኑም የኢትዮጵያ መንግስት የሠላም ንግግሩ እነዚህንና መሰል ጉዳዮችን ከግምት ውስጥ እንዲያስገባ እና አብን ጠይቋል።

በሳሙዔል ወርቃየሁ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.