Fana: At a Speed of Life!

ኢራን እና ሩሲያ የ6 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር የጋዝ ግዥ ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢራን እና ሩሲያ የ6 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር የጋዝ ግዥ ስምምነት መፈራረማቸው ተገለፀ፡፡

የኢራን ከፍተኛ ባለስልጣን ቴህራን፥ የሩሲያ ግዙፍ የነዳጅ አምራች ኩባንያ ከሆነው ጋዝፕሮም ጋር የ6 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር የጋዝ ግዥ ለማድረግ ውል መፈፀሟን አስታውቀዋል፡፡

በኢራን የውጭ ጉዳይ የኢኮኖሚክ ዲፕሎማሲ ምክትል ሚኒስትር መህዲ ሳፋሪ እንደገለፁት የጋዝ ግዥው ስምምነት ሀገራቱ ባለፈው ሐምሌ ወር የተፈራረሙት የ40 ቢሊየን ዶላር የመግባቢያ ስምምነት አካል ነው።

ባለፈው ሀምሌ ወር ፕሬዚዳንት ፑቲን ከኢራን እና ከቱርክ አቻዎቻቸው ጋር ለመወያየት ቴህራን በገቡበት ወቅት ኢራን እና ሩሲያ የ40 ቢሊየን ዶላር የነዳጅ ግዥ ስምምነት ለመፈፀም መስማማታቸው የሚታወስ ነው፡፡

ስምምነቱ በጋዝ መሰረተ ልማት በትብብር ለመስራትና የጋዝ ሽያጭና ግብይትን ለመፈጸም የሚያስችል እንደሆነ መገለጹ ይታወሳል።

ኢራን ከሩሲያ በመቀጠል በዓለም ሁለተኛዋ ትልቅ የጋዝ ክምችት ያላት ሀገር መሆኗን ፕረስ ቲቪ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.