Fana: At a Speed of Life!

የስራና ክህሎት እና የትምህርት ሚኒስቴር በትምህርት ስርዓት ዙሪያ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የስራና ክህሎት ሚኒስቴር እና የትምህርት ሚኒስቴር በትምህርት ስርዓት ዙሪያ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

የተፈረመው ስምምነት የትምህርት ስርዓቱ ሁለንተናዊ ክህሎት የሚያስገኝ እንዲሆንና ተቋማቱ በጋራ እንዲሰሩ ያስችላቸዋል ተብሏል፡፡

ስምምነቱን የተፈራረሙት የስራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል እና የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ ናቸው።

በስምምነት ስነ-ስርዓቱ ወቅት ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል እንደገለጹት÷ ከመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ጀምሮ ሊሰሩ የሚችሉ የአስተሳሰብ ጉዳዮችን ጨምሮ የተለያዩ ስራዎች ለመስራት መለየታቸውን አንስተዋል።

በስምምነቱ መሰረት አዲሱን የትምህርት ፍኖተ ካርታ በስርዓተ ትምህርቱ ለማካተት በሚሰራው ስራ የትምህርት ስርዓቱ ክህሎትን የሚያስገኝ እንዲሆን ይሰራልም ብለዋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ በበኩላቸው÷ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶቹ በጋራ መስራታቸው ዘርፈ ብዙ ጥቅም እንዳለው ገልጸዋል፡፡

የመግባቢያ ስምምነቱ ከትምህርት ጥራት ጋር የተያያዙ ስራዎችን ለመስራት እንደሚያስችልም ጠቁመዋል፡፡

ከትምህርት ጥራት ባለፈ ክህሎት ላይ መስራት እንደሚያስፈልግ ጠቅሰው÷ የትምህርት ስርዓቱን ማሻሻል ብቻ ሳይሆን ተማሪዎች በክህሎት የበቁ እንዲሆኑ ይሰራል ነው ያሉት፡፡

በቅድስት ብርሃኑ

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.