Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ይበልጣል ከሱዳን የኢሚግሬሽንና ፓስፖርት ጉዳዮች ዋና ዳሬክተር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሱዳን የኢፌዴሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ ከሱዳን የኢሚግሬሽንና ፓስፖርት ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄኔራል ሙኣዊያ ጀእፈር ጋር ተወያዩ፡፡

በውይይታቸውም÷ በሱዳን የሚኖሩ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው ኢትየጵያውያን እየገጠማቸው ያለውን ችግር በተመለከተ መክረዋል፡፡

በተሽከርካሪ ወደ ሀገራቸው መመለስ የሚፈልጉ ኢትጵያውያን የመውጫ ፈቃድ ክፍያ ሙሉ በሙሉ እንዲነሳ ይህ ካልተቻለ ደግሞ አቅማቸውን ያገናዘበ ማሻሸያ እንዲደረግላቸው ሲሉ አምባሳደር ይበልጣል ጠይቀዋል፡፡

ሜጀር ጄኔራል ሙኣዊያ ጀእፈር በበኩላቸው÷ ኤምባሲው ፓስፖርት ለሚሰጣቸው ኢትጵያውያን የመኖሪያ ፈቃድ ለማውጣት የሚያስችላቸው የስድስት ወር ጊዜ እንደሚሰጥ አረጋጠዋል፡፡

በተሽከርካሪ ወደ ሀገራቸው ለሚመለሱም በኤምባሲው በኩል ተመዝግበው ለሚቀርቡ ሰነድ አልባ ዜጎች በቅናሽ ክፍያ የመውጫ ፈቃድ ሊሰጥ እንደሚችል ገልጸዋል።

በሱዳን የሚኖሩ ኢትየጵያውያን ከሚያጋጥማቸው ችግር በዘላቂነት የሚላቀቁት ፓስፖርት በማውጣት ሕጋዊ የመኖሪያ እና የሥራ ፈቃድ ሲኖራቸው ብቻ መሆኑን እንዲገነዘቡ ሲል በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ አሳስቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.