Fana: At a Speed of Life!

ሰሜን ኮሪያ በዓመት ለሰባተኛ ጊዜ አህጉር አቋራጭ ሚሳኤል አስወነጨፈች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰሜን ኮሪያ አህጉር አቋራጭ የባላስቲክ ሚሳኤል በዓመት ውስጥ ለሰባተኛ ጊዜ ማስወንጨፏ ተሰምቷል፡፡

ሚሳኤሉ 760 ኪሎ ሜትር ርቀት መጓዙን የደቡብ ኮሪያ መከላከያን ዋቢ ያደረገው የቢቢሲ ዘገባ ያመላክታል።

ፒዮንግያንግ ከአህጉር አቋራጩ ባለስቲክ ሚሳኤል ባለፈም አጭር ርቀት ሚሳኤል ማስወንጨፏም ነው የተገለጸው።

የአሁኑ የሚሳኤል ሙከራ ሁለቱ ኮሪያዎች የእርስ በእርስ ሚሳኤል ካስወነጨፉ ከአንድ ቀን በኋላ የተደረገ ነው ተብሏል።’

በትናንቱ የሁለቱ ሀገራት የተኩስ ልውውጥ ሰሜን ኮሪያ በቁጥር በርከት ያሉ ሚሳኤሎችን ማስወንጨፏ ተመላክቷል፡፡

በቅርቡም የኒውክሌር መሣሪያ ሙከራ ሳታደርግ አትቀርም ነው የተባለው።

አሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ በጋራ የአየር ልምምድ ማድረጋቸውን ተከትሎ ሰሜን ኮሪያ “ይህ አግባብነት የሌለው ፀብ አጫሪ ድርጊት ነው “በማለት ስታወግዝ መቆየቷን ዘገባው አስታውሷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.