Fana: At a Speed of Life!

በሰሜን ዕዝ ላይ የተፈጸመው ጥቃት 2ኛ ዓመት በብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ታስቦ ዋለ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት አመራሮችና ሠራተኞች ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም በመከላከያ ሠራዊት ሰሜን ዕዝ ላይ የተፈጸመውን አሰቃቂ ጥቃት በማስመልከት የመታሰቢያ ሥነ ሥርዓት አካሂደዋል።

የመታሰቢያ መርሐ ግብሩ ፥  “ስለኢትዮጵያ የከፈላችሁትን አንረሳም” የሚል መሪ ቃል ነው በተለያዩ ዝግጅቶች የተካሄደው፡፡

የጥቃቱ መስዋዕትነት የከፈሉ የመከላከያ ሠራዊት እንዲሁም የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ተቋም አባላትን ለመዘከር የህሊና ጸሎት ፣ የሻማ ማብራትና የፓናል ውይይት ተካሂዷል ።

ዕለቱ የኢትዮጵያን ህልውና አደጋ ውስጥ በማስገባት ለውጭ የጠላት ኃይል ተጋላጭ እንድትሆን በመከላከያ ሠራዊት የሰሜን ዕዝን ዒላማ ያደረገ ጥቃት የተሰነዘረበትና ልዩ ትርጉም ያለው መሆኑም ነው የተመላከተው፡፡

በመርሐ ግብሩ የፀጥታና ደህንነት አካላት የሀገር ሉዓላዊነት እንዲከበር የከፈሉትንና እየከፈሉ ላሉት ውድ የህይወት መስዋትነት የላቀ ክብርና ምስጋና መስጠት እንደሚገባ  መገለጹንም ከአገልግሎቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.