Fana: At a Speed of Life!

በእስራዔል ምርጫ ቤኒያሚን ኔታንያሁ አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በእስራዔል በተካሄደው ምርጫ ቤኒያሚን ኔታንያሁ አሸናፊ ሆኑ።

የሀገሪቷ ማዕከላዊ የምርጫ ኮሚሽን ውጤቱን ይፋ አድርጓል።

እስራዔልን በጠቅላይ ሚኒስትርነት እስካሁን ሲመሩ የቆዩት ያይር ላፒድም ተፎካካሪያቸውን ጠርተው ውጤቱን እንደሚቀበሉት አረጋግጠውላቸዋል፡፡

ከዚህ በኋላ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ለመባል የሚበቁት ያይር ላፒድ ሥርዓታዊ ሽግግር ለማድረግ ቃል መግባታቸውን የእስራዔል ብዙኃን መገናኛ ዘግበዋል፡፡

የቅድመ ምርጫው ውጤቶች እንዳመላከቱት ÷ የኔታንያሁ ጥምር ፓርቲ በፓርላማው ውስጥ ካሉት 120 መቀመጫዎች 64ቱን መሰብሰብ ችሏል፡፡

ያይር ላፒድ ደግሞ 51 መቀመጫዎችን አግኝተዋል ነው የተባለው፡፡

ዝርዝር የምርጫ ውጤቶች መረጃ እስከሚቀጥለው ሳምንት ድረስ ይወጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ የአር ቲ ዘገባ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.