Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት 3 ወራት ከቡና ሻይና ቅመማቅመም 428 ሚሊየን ዶላር ገቢ ተገኘ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ሶስት ወራት ከቡና ሻይና ቅመማቅመም 428 ሚሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱን የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡

ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ የ2015 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የሥራ አፈፃፀሙን በጎንደር ከተማ እገመገመ ነው።

በመድረኩ የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ እደተናገሩት ÷ የቡና ሻይና ቅመማቅመም ምርትን ጥራት ለማሳደግና ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለመጨመር ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው።

ከውጪ ንግድ ግብይት ከተገኘው ገቢ የቡና ድርሻ 426 ሚሊየን ዶላሩን እንደሚሸፍን ነው ዳይሬክተሩ ያስረዱት።

በቀጣይ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በክልሎች መካከል የልምድ ልውውጥ ለማካሄድ በትኩረት እንደሚሰራም ተመላክቷል፡፡

በክብረወሰን ኑሩ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.