Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ እና ደቡብ ኮሪያ መካከል የድሮን ካርታ ስራን ማስፋፋት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 26 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮሪያ የአቪዬሽን ደህንነት ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ከኢፌዴሪ ከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ጋር በኢትዮጵያ የድሮን ካርታ ስራን ለማስፋፋት የሚያስችል ስምምነት ተፈራርሟል።

ስምምነቱ በድሮን ላይ የተመሰረቱ የካርታ አገልግሎቶችን እና ከፍተኛ የክህሎት ሽግግር ስራዎችን ወደ ኢትዮጵያ እንደሚያመጣ እና ውጤታማ የለውጥ መሳሪያ የመሆን ሃይል እንዳለው ተገልጿል።

ፕሮጀክቱን የሚመራው በኮሪያ ድሮን ላይ የተመሰረተ የጂኦማቲክ እና የዳሰሳ ጥናት ባለሙያዎች ሆጁንግ ሶሉሽንስ የተባለ ተቋም ነው።

የሆጁንግ ምክትል ፕሬዚዳንት አንድሪው ቾ በስምምነቱ ወቅት እንዳሉት ይህ የመግባቢያ ሰነድ የድሮን ክህሎቶችን ፣ የደህንነት ማዕቀፎችን እና በድሮን መተግበሪያዎች ውስጥ ቀጣይነት ያለው እድገትን ለመፍጠር እና በቀጣይ የትብብር ስራዎችን ለመጀመር ያስችላል።

በደቡብ ኮሪያ እየተካሄደ ባለው የስማርት ጂኦ እስፓሺያል አውደርዕይ ላይ ከተለያዩ ሀገራት የእስፓሺያል መረጃዎች አሰባሰብ እና አያያዝ ላይ ተምክሮዎች ቀርበዋል።

በኢፌዴሪ ከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር የመሬትና ካዳስተር ስራ አስፈፃሚ አቶ ብዙዓለም አድማሱ በመድረኩ ላይ ሀገራችን ያለችበትን ደረጃና ለሌሎች ልምድ የሚሆኑ እንዲሁም ቀጣይ መሠራት ያለባቸው ስራዎችን ማብራራታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.