Fana: At a Speed of Life!

የሰላም ስምምነቱን አስመልክቶ በኢትዮጵያ ለሚገኙ ዲፕሎማቲክ ማህበረሰቦች ገለፃ ተደረገ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 26 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በፌደራል መንግስትና ህወሓት መካከል የተደረገውን የሰላም ስምምነት አስመልክቶ በኢትዮጵያ ለሚገኙ ዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት ገለፃ ተደረገ።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ሚኒስትር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ገለፃ አድርገዋል።

ለስምምነቱ የአፍሪካ ህብረት ትልቅ ሚና መጫወቱን ያነሱት አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በሰላም ስምምነቱ ከስምምነት ላይ የተደረሰባቸውን ጉዳዮች በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የተኩስ ማቆም፣ ትጥቅ ማስፈታት፣ በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ማቋቋም፣ መሰረታዊ አገልግሎት ማስጀመር እና መልሶ ግንባታን የመሳሰሉ ጉዳዮች በስምምነቱ የተካተቱ ውሳኔዎች ወደ ተግባር ለመቀየር ሁለቱ ወገኖች ዝግጁ መሆናቸወንም አንስተዋል።

መንግስት ለሰላም ስምምነቱ ተግባራዊነት እየሰራ ነው ያሉት አምባሳደር ሬድዋን ወዳጅ ሀገራት የሰላም ስምምነቱን እየደገፉት መሆኑንም ተናግረዋል።

መንግስት የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ ለመገንባት በሙሉ አቅሙ ይሰራል ሲሉም ወዳጅ ሀገራት በመልሶ ግንባታው ከመንግስት ጎን እንዲቆሙ ጠይቀዋል።

በታሪኩ ለገሰ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.