Fana: At a Speed of Life!

የዲፕሎማቶች ስልጠና ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ያተኮረ የዲፕሎማቶች ስልጠና በአፍሪካ የአመራር ልህቀት አካዳሚ ተጀምሯል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ስልጠናውን ባስጀመሩበት ወቅት እንደገለጹት÷ ሥልጠናው በዲፕሎማሲ ባህልና ታሪክ ፣ በዓለም አቀፍ ግንኙነት እና ሥርዓት ውስጥ ያሉ ወቅታዊ የዲፕሎማሲ ተግባራት ላይ ያተኮረ ነው፡፡

ኢትዮጵያ የተለያዩ የዲፕሎማሲ ጫናዎች ውስጥ መሆኗን ጠቅሰው ፥ ዲፕሎማቶች ወቅቱን ያገናዘበ የዲፕሎማሲ ሥራ ሊያከናውኑ ይገባል ብለዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት የዲጅታል ዲፕሎማሲ ስራን ማጠናከር ፣ እውነትን እና ሀቅን በመያዝ የተለያዩ አካላት ተፅዕኖ በመቋቋም ተልዕኮውን በአግባቡ የሚወጣ ዲፕሎማት እንደሚያስፈልግ ነው የገለጹት፡፡

አምባሳደር ብርቱካን ፥ የዲፕሎማቶችን ብቃት ለማሳደግ የሰው ኃይል ልማት ሥራ፣ የውጭ አገልግሎት አዋጅ ማሻሻያና ብዝሃነትን ያገናዘበ ምርጫ በማድረግ አቅምና ብቃት በመጨመር የበለጠ የመፈፀም አቅማችን እያጠናከርን ነው ብለዋል ።

በቀጣናው ሰላም እንዲኖር ለማስቻል ብቁነትን ማጎልበትና እውቀትን ማሳደግ በሚቻልበት ዙሪያ አውዱ የሚጠይቀውን ኃላፊነት መወጣት ይገባል ነው ያሉት፡፡

የአፍሪካ የአመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዚዳንት ምህረት ደበበ በበኩላቸው፥ ከዚህ በኋላ በዲፕሎማሲ ሥራዎች የምንበረታበት ጊዜ ነው ብለዋል፡፡

በዚህ ወቅት ኢትዮጵያ ዘርፈ ብዙ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት እንደሚያስፈልጋትም በአጽንኦት መግለጻቸውንም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.