Fana: At a Speed of Life!

በኤሌክትሪክ አገልግሎት የህብረተሰቡን እርካታ ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው-አቶ ሽፈራው ተሊላ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኤሌክትሪክ አገልግሎት የህብረተሰቡን እርካታ ለማሳደግ በትኩረት እየሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎ ዋና ስራ አስጻሚ አቶ ሽፈራው ተሊላ ተናገሩ፡፡

በአገልግሎቱ የቀጣይ 3 ዓመታት ስትራቴጂክ ዕቅድ ላይ የሚመክር ሀገር አቀፍ የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ፎረም እየተካሄደ ነው።

የአገልግሎት አሰጣጡን ተወዳዳሪና ደንበኛ ተኮር ለማድረግ የሚያግዘውና ከ2015 እስከ 2017 ዓ.ም ድረስ የሚተገበር አዲስ ስትራቴጂ እያስተዋወቀም ይገኛል፡፡

በመድረኩ ላይ የተገኙት የአገልግሎቱ ዋና ስራ አስጻሚ አቶ ሽፈራው ተሊላ÷ የህብረተሰቡን ፍላጎት በሚሰጠው አገልግሎትር ለማርካት የለውጥ ስራዎች ላይ ትኩረት አድርጓል ብለዋል።

በተለይም ቴክኖሎጂን በመጠቀም አገልግሎት መስጠት ላይ እየተሰራ መሆኑ ጠቁመው÷ የጸሃይ ሃይልን በመጠቀም ተደራሽነቱን ለማሳደግ እንቅስቃሴ ተጀምሯል ነው ያሉት።

በቀጣይም አገልግሎቱን የበለጠ ተደራሽ ለማድረግ የሶስት ዓመት ስትራቴጂክ እቅድ ተከልሶ ወደ ስራ እንደገባ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የኤሌክሪክ አገልግሎት ለህዝቡ በአስተማማኝ ደረጃ ተደራሽ በማድረግ ረገድ የሚዲያና ኮሚኒኬሽን ዘርፉ ትልቅ ሚና አለው ያሉት ዋና ስራ አስጻሚው÷ በዚህ ዙሪያ በቅንጅት መስራት እንደሚያስፈልግ ጠቅሰዋል።

በፎረሙ ከተለያዩ የመንግስትና የግል መገናኛ ብዙሃን የበላይ ኃላፊዎች እንዲሁም የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች የኮሙኒኬሽን አመራሮች ተሳትፈዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.