Fana: At a Speed of Life!

በጥሎ ማለፉ ሊቨርፑል ከሪያል ማድሪድ እንዲሁም ባየር ሙኒክ ከፒ ኤስ ጂ ይጫወታሉ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 28 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ ዕጣ ድልድል ይፋ ሆኗል።

ከየምድባቸው 1ኛ እና 2ኛ ሆነው ያጠናቀቁ ቡድኖችን በሚያገናኘው ጥሎ ማለፍ 16 ቡድኖች ሩብ ፍጻሜውን ለመቀላቀል የደርሶ መልስ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

የአምናውን የውድድሩ አሸናፊ ሪያል ማድሪድ ከሊቨርፑል እንዲሁም የጀርመኑን ሃያል ክለብ ባየር ሙኒክ ከፈረንሳዩ ፒ ኤስ ጂ ያገናኘው ድልድል ከወዲሁ ተጠባቂ ሆኗል።

ኤሲ ሚላን ከእንግሊዙ ቶተንሃም ሆትስፐርስ እንዲሁም ቦሩሲያ ዶርትመንድ ከቼልሲ የሚያደርጉት ጨዋታም ጠንካራ ፉክክር የሚታይባቸው ተጠባቂ ጨዋታዎች ናቸው።

በሌሎች ድልድሎች የቤልጂየሙ ክለብ ብሩጅ ከፖርቹጋሉ ቤኔፊካ እንዲሁም የጀርመኑ ኤይንትራክት ፍራንክፈርት ከጣሊያኑ ናፖሊ ይጫወታሉ።

የእንግሊዙ ሻምፒዮን ማንቼስተር ሲቲ ከአር ቢ ሌፕዚግ ሲገናኝ የጣሊያኑ ኢንተር ሚላን ከፖርቹጋሉ ፖርቶ የሚጫወት ይሆናል።

የደርሶ መልስ ጨዋታዎቹ የፊታችን የካቲት አጋማሽ እና በመጋቢት ወር የመጀመሪያዎቹ ቀናቶች ይደረጋሉ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.