Fana: At a Speed of Life!

ሰሜን ኮሪያ ለሩሲያ ምንም አይነት የጦር መሳሪያ ድጋፍ አለማድረጓን አስታወቀች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጦር መሳሪያ ለሩሲያ ረድታለች በማለት አሜሪካ ያቀረበችውን ክስ መሰረተቢስ ነው ስትል ሰሜን ኮሪያ ምላሽ ሰጥታለች፡፡

ሰሜን ኮሪያ ይህንን ያለችው ባለፈው ሳምንት ዋሺንግተን ሩሲያ ከዩክሬን ጋር በገባችው ግጭት የምታደርገውን ዘመቻ ለመደገፍ ሰሜን ኮሪያ በድብቅ የጦር መሳሪያ ልካለች ማለቷ ይታወሳል።

ይህንን ተከትሎም ሞስኮ ውንጀላው አግባብነት የሌለው እና መሰረተ ቢስ ነው በሚል አስተባብላለች።

ሰሜን ኮሪያም የአሜሪካ ውንጀላ መሰረተ ቢስ እና ስም ለማጠልሸት የተደረገ ነው በሚል የቀረበባትን ክስ ውድቅ አድርጋለች።

ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ አንድ የሰሜን ኮሪያ የመከላከያ ባለስልጣን አሜሪካ መሰረተ ቢስ ወሬ እያሰራጨች መሆኑን ገልጸዋል።

አሜሪካ እንዲህ አይነት ተጨባጭ ያልሆኑ ውንጀላዎች የምታሰራጨው በጸጥታው ምክር ቤት የቅጣት ውሳኔ በማስወሰን በዓለም አቀፉ መድረክ የሀገሪቱን መልካም ገጽታ ለማበላሸት በማሰብ ነው ሲሉም ለአሜሪካ ውንጀላ ጠንከር ያለ ምላሽ ሰጥተዋል።

ከሩሲያ ጋር የጦር መሣሪያ ግንኙነት ፈጽሞ እንዳልነበረን እና ወደፊትም ይህን ለማድረግ እቅድ እንደሌለን በድጋሚ በግልጽ ሊታወቅ ይገባል ማለታቸውን አር ቲ ዘግቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.