Fana: At a Speed of Life!

አርቲስት ዓሊ በሥራዎቹ ሰላምን እና አንድነትን ሰብኳል- አቶ አደም ፋራህ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አርቲስት ዓሊ ቢራ በሥራዎቹ ግጭትን ሳይሆን ሰላምን፤ እኔን ሳይሆን እኛን በማለት ሙያውን ያስተማረ የሀገር ባለውለታ ነበር ሲሉ አቶ አደም ፋራህ ገለጹ፡፡

የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ በወዳጅነት ዐደባባይ በተካሔደው የአርቲስት ዓሊ ቢራ የአስከሬን ሽኝት ሥነ ስርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር÷ አርቲስት ዓሊ በሥራዎቹ ግጭትን ሳይሆን ሰላምን፤ ተስፋ መቁረጥን ሳይሆን ጽናትን፤ እኔን ሳይሆን እኛን በማለት ሙያውን በሚገባ ተጠቅሞ በማስተማር ሀገራዊ ውለታ አበርክቷል ነው ያሉት።

የድሬዳዋ ልጅነት መገለጫ የሆኑ ዕሴቶች በሙሉ የተላበሰ ነበር ያሉት አቶ አደም÷ ሩህሩህ፣ ያለውን ሁሉ የሚሰጥ፣ ሰውን በሰውነቱ ብቻ የሚያከብር እና የሚወድ የፍቅር ሰው ነበር ብለዋል፡፡

በሠራቸው ድንቅ ሥራዎች እና በመልካም ሰብዕናው በሁሉም ዘንድ የሚከበር፣ የሚወደድ እና የሚደነቅ ታላቅ የጥበብ ሰው እንደነበርም ገልጸዋል፡፡

ለባለቤቱ፣ ለዘመዶቹ ፣ ለአድናቂዎቹ እና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡

በዮሐንስ ደርበው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.