Fana: At a Speed of Life!

የአርቲስት ዓሊ ቢራ የአስከሬን ሽኝት ሥነ ስርዓት በትውልድ ሥፍራው እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአርቲስት ዓሊ ቢራ የአስከሬን ሽኝት ሥነ ስርዓት በትውልድ ሥፍራው ድሬዳዋ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

የአርቲስት ዓሊ አስከሬን ዛሬ ከቢሾፍቱ ወደ አዲስ አበባ ወዳጅነት ዐደባባይ እና ከወዳጅነት ዐደባባይ ወደ ድሬዳዋ ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች፣ ቤሰቦቹ፣ የሙያ አጋሮቹ እዲሁም አድናቂዎቹ በተገኙበት ተሸኝቷል፡፡

አሁን ደግሞ ሥርዓተ ቀብሩ በሚፈጸምበት የትውልድ ስፍራው ድሬዳዋ ከተማ የሽኝት ሥነ ስርዓት እየተካሔደ ነው፡፡

በሽኝት ሥነ ስርዓቱ ላይ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሐይማኖት አባቶች እንዲሁም የአርቲስት ዓሊ ቢራ አድናቂዎችና ወዳጆች ተገኝተዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.