Fana: At a Speed of Life!

በሰበታ ከተማ በአርቲስት ዓሊ ቢራ ስም ትምህርት ቤት ተሰየመ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰበታ ከተማ አስተዳደር የሚገኝ ትምህርት ቤት በአርቲስት ዓሊ ቢራ ስም መሰየሙን የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት አስታውቋል።

በኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወሉ አብዲ የተመራ የልኡካን ቡድን በሰበታ ከተማ አስተዳደር ቡዑራ ቦሩ ት/ቤት የተማሪዎች ምገባ ስነ ስርዓት ይፋ አድርጓል፡፡

በዚህ ወቅት ትምህርት ቤቱ ስያሜውን በአርቲስት ዓሊ ቢራ እንዲሆን ማድረጉን መገለፁን ከኦሮሚያ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

አርቲስት ዓሊ ቢራ ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ ለነፃነት፣ወንድማማችነት፣አንድነት እና ትምህርትን ጨምሮ የተለያዩ ይዘት ያላቸው በርካታ ሙዚቃዎችን በማበርከት ከዚህ ዓለም ተለይቷል።

ለአርቲስቱ በዛሬው ዕለት በወዳጅነት አደባባይ ደማቅ የጀግና አሸኛኘትም ተደርጎለታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.