Fana: At a Speed of Life!

ዓለም አቀፍ የሳይንስ ቀን አስመልክቶ በተማሪዎችና መምህራን የፈጠራ ስራ ውድድር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት ሚኒስቴርና አጋር ድርጅቶች በመተባበር ለ7ኛ ጊዜ የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የሳይንስ ቀን አስመልክቶ በተማሪዎችና መምህራን መካከል የፈጠራ ስራ ውድድር አካሂደዋል።

ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎችና የክልል 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ መምህራንና ተማሪዎች የፈጠራ ስራዎቻቸውን ለዳኞች ገለጻ በማድረግ አስገምግመዋል።

የውድድሩ ውጤትም በአውደ ርእዩ መዝጊያ ወቅት እንደሚገለጽና ከየምድቡ ከአንድ እስከ ሦስት ለወጡ ተወዳዳሪዎች የማበረታቻ ሽልማት እንደሚበረከትላቸው ተገልጿል።

አውደ ርዕዩም በነገው እለት ለህዝብ ክፍት እንደሚሆን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በዚህም ማንኛውም መጎብኘት የሚፈልግ አካል አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ በመገኘት መጎብኘት እንደሚችልም ነው የተገለጸው።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.