Fana: At a Speed of Life!

የአንጋፋው አርቲስት ዓሊ ቢራ ስርዓተ ቀብር ተፈፀመ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአንጋፋው የጥበብ ሰው አርቲስት ዓሊ ቢራ የቀብር ሥነ ስርዓት በድሬዳዋ ከተማ ተፈፀመ፡፡

አርቲስት ዓሊ ቢራ ከአባቱ አቶ መሐመድ ሙሣ እና ከእናቱ ወይዘሮ ፋጡማ ዓሊ በ1940 ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ገንደ ቆሬ እንደተወለደ የሕይወት ታሪኩ ያስረዳል፡፡

ባለፉት 60 ዓመታትም ለሙያው ታምኖ የኖረው ዓሊ÷ ከድሬዳዋ እና ጅማ ዩኒቨርሲቲዎች የክብር ዶክትሬት ተበርክቶለታል፡፡

አርቲስቱ ባጋጠመው ሕመም ምክንያት በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ ጥቅምት 27 ቀን 2015 ዓ.ም በተወለደ በ75 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡

ዛሬ ጠዋት የአርቲስቱ አስክሬን ቢሾፍቱ ከሚገኘው መኖሪያ ቤት ሽኝት የተደረገለት ሲሆን÷ በአዲስ አበባ ወዳጅነት አደባባይም የጀግና የክብር ሽኝት ተደርጎለታል፡፡

እንዲሁም በድሬዳዋ ስታዲየም የሽኝት መርሐ ግብር ከተካሄደ በኋላ የቀብር ሥነ ስርዓቱ በለገሀሬ የሙስሊም መካነ መቃብር ተፈፅሟል፡፡
አርቲስት ዓሊ ቢራ ከወይዘሮ ሊሊ ማርቆስ ጋር ትዳር መስርቶ ይኖር ነበር፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.