Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ ውሳኔዎችን አሳለፈ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ በ2ኛ አመት 5ኛ መደበኛ ስብሰባው የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡

በዚህም መሰረት ፥ የጥቁር ህዝቦች ነፃነትና የጀግንነት ማሳያ አርማ የሆነው የአድዋ ሙዚየም የኪነጥበብ ስራ ላይ ተወያይቶ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ተወክለው ግብዓቶችን እንዲሰጡበት አቅጣጫ ሰጥቷል፡፡

በተጨማሪም የመልካም አስተዳደር ችግር ሆኖ የቆየውን የግንባታ ጊዜያቸው ያለፈባቸውን 1 ሺህ 44 ፕሮጀክቶች በአብዛኛው የመኖርያ ቤቶች በመሆናቸው ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የግንባታ ጊዜያቸው እንዲራዘምላቸው ወስኗል፡፡

በሌላ በኩል ቢሮ ለሌላቸው 11 ወረዳዎች በፈጣን የግንባታ ስልት 11 ህንፃዎች እንዲገነቡ መወሰኑን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የቃሊቲ ቱሉ ዲምቱ ቀለበት መንገድ ግንባታ ለማጠናቀቅ የኤግዚም ባንክ ብድር እስከሚለቀቅ ድረስ ከመንግስት በጀት በብድር መልክ ክፍያ እየተፈፀመ ፕሮጀክቱ እንዲጠናቀቅም ነው ካቢኔው የወሰነው፡፡

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.