Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ እና ሩሲያ በይደር ያቆዩትን የኒውክሌር ጦር መሣሪያ ቅነሳ ድርድር ሊጀምሩ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ እና ሩሲያ የኒውክሌር ጦር መሣሪያ ቅነሳ ላይ ለመምከር ሊገናኙ ነው።

የአሜሪካ እና የሩሲያ ዲፕሎማቶች በቅርብ ጊዜ ውስጥ በግብፅ እንደሚገናኙ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ መናገራቸውን አር ቲ የአሜሪካ የዜና ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡

የሁለትዮሽ ውይይቶቹ ኒውክሌር የሚያደርሰውን አደጋ ለመቀነስ ሊወስዱ በሚገባቸው እርምጃዎች ላይ ያተኮሩ እንደሆኑም ተጠቅሷል፡፡

ምንም እንኳን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ ውይይቱ የሚካሄድበትን ትክክለኛ ቦታ ለጊዜው ባይጠቁሙም ግብፅ ለሁለቱ ሀገራት ካላት ገለልተኛ አቋም አንጻር ልትመረጥ እንደምትችል አር ቲ ብሉምበርግን ጠቅሶ ፅፏል፡፡

ብሉምበርግ መላምቱን ሲያስቀምጥም አሜሪካ እና የአውሮፓ ኅብረት በዩክሬን ጉዳይ ላይ ባላቸው አቋም እና ሩሲያ ላይ በጣሉት ማዕቀብ ምክንያት ድርድሩ ጄኔቫ ላይ ይካሄድ ቢባል ሞስኮ ፈፅሞ አትቀበልም፡፡

በፈረንጆቹ ጥቅምት 2021 አሜሪካ እና ሩሲያ ጄኔቫ ላይ ተገናኝተው የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ቁጥጥር ስምምነት መድረሳቸው የሚታወስ ነው።

ይህ ስምምነት በድጋሚ ካልታደሰ በፈረንጆቹ 2026 የአገልግሎት ጊዜው ያበቃል ነው የተባለው።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.