Fana: At a Speed of Life!

አቶ አወል አርባ በዱብቲ ወረዳ የተከናወኑ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕስ መስተዳድር አወል አርባ በዱብቲ ወረዳ አውሲ ረሱ የጎርፍ አደጋን ለመካለከል እየተሠሩ የሚገኙ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል፡፡

አቶ አወል እየተሠሩ ከሚገኙ የመሠረተ ልማት ሥራዎች በተጨማሪ በአካባቢው እየለማ የሚገኘውን የስንዴ ማሳ መመልከታቸውን የርዕሰ መስተዳድር ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

ከጉብኝታቸው በኋላ ወረዳው ለጎርፍ አደጋ እንዳይጋለጥ እየተሠራ ያለው የቅድመ ጥንቃቄ ሥራ በተያዘው ፍጥነት እንዲጠናቀቅ አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡

እንዲሁም በዱብቲ ወረዳ በስንዴ እየለማ የሚገኝ ማሳን በጎበኙበት ወቅት እንደገለጹት÷ ሕዝቡ ያለውን ለም መሬት በመስኖ በመጠቀም የግብርና ሥራውን ሊያስፋፋ ይገባል፡፡

ለዚህም የክልሉ መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.