Fana: At a Speed of Life!

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳይ ላይ እየተወያዩ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎች በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳይ ዙሪያ ውይይት ማካሄድ ጀመሩ።

በውይይቱ ላይ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የዞንና የከተማ አስተዳደር የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።

ውይይቱ የኢትዮጵያ መንግስት ከሕወሓት ጋር በደቡብ አፍሪካ የደረሠው የሠላም ስምምነት ላይ ትኩረት ያደረገ ነው ተብሏል፡፡

የክልሉ ብልጽግና ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢስሃቅ አብዱልቃድር፥ መንግስት ከሕወሓት ጋር የደረሠውን የሠላም ስምምነት ሂደት፣ ውጤትና ጠቀሜታ ያካተተ መነሻ ሠነድ ማቅረባቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በሠነዱም ድሉ በመስዋዕትነት የተገኘ ድል በመሆኑ፣ ከፍተኛ ዋጋ የሚሠጠው መሆኑ ተጠቅሷል ነው የተባለው።

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.