Fana: At a Speed of Life!

ዓለም አቀፍ የማዕድን ኤክስፖ ተከፈተ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፍ የማዕድን ኤክስፖ “Mintex” በሚሊንየም አዳራሽ ተከፍቷል፡፡

ከዛሬ ጀምሮ እስከ ህዳር 3 ቀን 2015 ዓ.ም በሚካሄደው ኤክስፖ ከ270 በላይ የሀገር ውስጥና የውጪ ኩባንያዎች ይሳተፋሉ።

የማዕድን ኩባንያዎች፣ የጌጣጌጥ አምራቾችና ላኪዎች፣ የማዕድን ቴክኖሎጂ አምራቾችና አስመጪዎች እንዲሁም የፋይናንስ ተቋማት ይሳተፋሉ።

ኤክስፖው አምራቾችን ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ ገዢዎች ጋር በቀጥታ ያገናኛል ነው የተባለው።

እንዲሁም ከውጪ የሚመጡ የማዕድን ኩባንያዎች በኤክስፖው ላይ መሳተፋቸው በኢትዮጵያ ያለውን የማዕድን ኢንቨስትመንት አማራጭ እንዲመለከቱና የማዕድን ኢንቨስትመንት ላይ እንዲሳተፉ እድል እንደሚፈጥር ተገልጿል፡፡

በዚህ ኤክስፖ የማዕድን ቴክኖሎጂ አምራቾች መሳተፋቸው ደግሞ ለኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ አዳዲስ የቴክኖሎጂ አማራጮችን የማስተዋወቅ እድል ይፈጥራል መባሉት ከማዕድን ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በመክፈቻ ሥነ ስርዓቱ ላይ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ የማዕድን ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ፣ ሚኒስትሮች፣ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.