Fana: At a Speed of Life!

ዶ/ር ይልቃል ከፋለ የታችኛው ርብ የመስኖ ልማት ፕሮጀክት የግንባታ ሂደትን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ እና ምክትል ርዕሰ መሥተዳድር ዶክተር ጌታቸው ጀምበርን ጨምሮ የክልልና የዞን ከፍተኛ አመራሮች የታችኛው ርብ መስኖ ልማት ፕሮጀክት የግንባታ ሂደትን ተመልክተዋል።

በደቡብ ጎንደር ዞን የሚገኘው ይህ ፕሮጀክት የመጀመሪያ ዙር ግንባታ ሲጠናቀቅ 3 ሺህ 100 ሄክታር መሬት በመስኖ ለማልማት እንደሚያስችል በጉብኝቱ ወቅት ተገልጿል።

ፕሮጀክቱ የካቲት 2013 ዓ.ም በዓባይ ኮንስትራክሽን ተጀምሮ ሰኔ 30 ቀን 2014 ዓ.ም ለማስረከብ ውል የተያዘ ቢሆንም አፈጻጸሙ ግን ከ21 በመቶ በላይ አለመከናወኑ ነው የተገለጸው፡፡

ካሳ የተከፈላቸው አርሶ አደሮች በጊዜ አለመነሳት እና የሥራ ተቋራጩ ድርጅት የአቅም ውስንነትን ለመዘግየቱ በምክንያትነት ተጠቅሷል።

በግንባታ ላይ ሆኖ ለአርሶ አደሮች መስኖ ልማት አጋዥ የሚሆን ውኃ እንዲለቀቅ ጥረት እየተደረገ ስለመሆኑም በመስክ ምልከታው ወቅት መገለጹን አሚኮ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.