Fana: At a Speed of Life!

የሰብዓዊ እርዳታውን በአፋጣኝ ለማድረስ የሚያግዙ 4 ቡድኖች ተዋቅረው ስራ ጀምረዋል-የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን የሰብዓዊ እርዳታን በአፋጣኝ ለማድረስ የሚያግዙ እና የሚያስተባብሩ አራት ቡድኖች ተዋቅረው ስራ መጀመራቸውን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ፡፡
 
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል።
 
በመግለጫቸውም የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ የተለያዩ የሰብዓዊ ድጋፍ እና የመልሶ ግንባታ ስራዎች በተለያዩ አካባቢዎች እየተከናወኑ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡
 
ቀድም ብሎ የሰብዓዊ እርዳታ ለማድረስ ከሚውለው የአፋር አብዓላ ኮሪደር በተጨማሪ በሰሜን ጎንደር በኩል የሽረ እና አጎራባች ወረዳዎች እንዲሁም በሰሜን ወሎ ቆቦ – አላማጣ የሚያደርሱ የሰብአዊ ድጋፍ ማቅረቢያ መስመሮች መዘርጋታቸውን ሚኒስትር ዴኤታዋ ተናግረዋል፡፡
 
ከሰላም ስምምነቱ ወዲህ 108 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የምግብ ድጋፍ መደረጉን ያነሱት ሚኒስትር ዴኤታዋ፥ ከ16 ሺህ በላይ ኩንታል ስንዴ ደግሞ ማቅረብ እንደተቻለ መናገራቸውን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.