Fana: At a Speed of Life!

በአቶ ሙስጠፌ የተመራ ልዑክ በቦቆልማዮ መልካዲዳ የሚገኙ ስደተኞችን ጎበኘ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ የተመራ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሥራ ኃላፊዎች ልዑክ በሊበን ዞን በቦቆልማዮ መልካዲዳ አካባቢ የሚገኙ ስደተኞችና የአካባቢው ነዋሪዎችን ሁኔታ ጎበኘ፡፡

የጉብኝቱ ዓላማ አካባቢው ዝናብ አጠር በመሆኑ መንግሥትና ግብረሰናይ ድርጅቶች የሚያደርጉትን ድጋፍ ለማፋጠን መሆኑን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

የልዑካን ቡድኑ አባላት ከሊባን ዞን አመራሮች እና በአካባቢው ከሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች ጋር ባደረጉት ውይይት÷ በድርቅ ለተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎች እንዲሁም በመልካዲዳ የስደተኞች ጣቢያ ለሚገኙ ወገኖች አስቸኳይ እርዳታ ለማድረስ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.