Fana: At a Speed of Life!

ከ140 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ140 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዛቸውን የጉምሩክ ኮሚሽን ገለጸ፡፡

ኮሚሽኑ ከጥቅምት 25 ቀን እስከ ሕዳር 1 ቀን 2015 ዓ.ም ባደረገው ክትትል 92 ነጥብ 6  ሚሊየን የገቢ ኮንትሮባንድ እቃዎች እና 49 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር በላይ የወጪ እቃዎች በአጠቃላይ 140 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በተለያዩ  ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች መያዛቸውን ገልጿል፡፡

ከተያዙት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል አልባሳት፣ ነዳጅ፣ የቁም እንስሳት፣ ኤሌክትሮኒክ፣ ቡና፣ መድሐኒት፣ የግንባታ እቃዎች፣ ተሽከርካሪዎች፣ የጦር መሳሪያዎች፣ አደንዛዥ እጾች፣ የምግብ ዘይት እና የተለያዩ ሀገር ገንዘቦች ይገኙበታል ተብሏል፡፡

የገቢ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር ረገድ ቀዳሚውን ስፍራ የሚይዙት ጅግጅጋ፣ ድሬዳዋ እና ሐዋሳ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች መሆናቸውም ተጠቅሷል፡፡

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች፣ በፌደራል ፖሊስ፣ በክልል ፖሊስ አባላትና ህብረተሰቡ ባደረጉት የጋራ ጥረት በፍተሻ፣ በብርበራና በጥቆማ መያዛቸውንም ከጉምሩክ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የኮንትሮባንድ እቃዎቹን ሲያዘዋውሩ የተገኙ 25 ግለሰቦች እና ዘጠኝ ተሽከርካሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋልም ነው የተባለው፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.