Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅትን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅትን ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝቱ÷ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የተለያዩ ሚኒስትሮች እና ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ለሀገር ዕድገትና ብልጽግና አስተዋጽዖ የሚያደርጉ አዳዲስ መፍትሔዎችን በማቅረብ ሀገራዊ ኢኮኖሚውን ለማሳደግ እየሠራ መሆኑንን የአገልግሎቱ መረጃ አመላክቷል፡፡

ከሎጂስቲክስና ፖስታ አገልግሎት በተጨማሪ የኢትዮጵያ ፖስታ በቅርቡ ወደ አህጉሪቱ ለሚገቡ ዕቃዎች ማዕከልነት የሚያገለግል የትራንዚት ኢ-ኮሜርስ አገልግሎት መጀመሩም ተመላክቷል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.