Fana: At a Speed of Life!

የዳያስፖራውን ሁሉአቀፍ ተሳፎ የሚያሳድጉ ሥራዎችን ለማከናወን ዝግጁ ነኝ- ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት የኢትዮጵያ ቢሮ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት በሚያቀርበው ጥያቄ መሰረት የዳያስፖራውን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተሳትፎ የሚያሳድጉ ሥራዎችን ለማከናወን ዝግጁ መሆኑን የዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት የኢትዮጵያ ቢሮ አስታወቀ፡፡

የዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት የኢትዮጵያ ቢሮ እና የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት የዳያስፖራውን ተሳትፎ ለማሳደግ በጋራ መስራት በሚችሉበት ጉዳይ ላይ መክረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር መሐመድ እንድሪስ አገልግሎቱ በኢትዮጵያ ለዳስፖራ ተሳትፎ የተዘረጉ ህጋዊና መዋቅራዊ መደላድሎች ይበልጥ ውጤታማ የሚሆኑበት መንገድ ከማመቻቸት አንጻር÷ ከዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት (አይ ኦ ኤም) ጋር ያለውን ግንኙነት በማጠናከር መስራት ይፈልጋል ብለዋል፡፡

ድርጅቱ ተሞክሮውን ተጠቅሞ የዳያስፖራውን አቅምና በሀገር ቤት ያለውን ፍላጎት ማጣጣም የሚያስችል ስትራቴጂ ለመቅረጽና የዳያስፖራ ተሳትፎን ሊያፋጥኑ የሚችሉ የአሰራር ስርዓቶችን በማበጀት ረገድ አገልግሎቱ የያዛቸውን ውጥኖች ዕውን ለማድረግ በጋራ መስራት እንደሚፈለግም ጠቅሰዋል።

በኢትዮጵያ የአይ ኦ ኤም ቢሮ ኃላፊ አቢባቱ ዋኔም በበኩላቸው÷ ድርጅታቸው አከገልግሎቱ ጋር ያለውን ግንኙነት አጠናክሮ ለመቀጠል ፍላጎት እንዳለው አረጋግጠዋል፡፡

ድርጅቱ በአገልግሎቱ በሚቀርቡ ጥያቄዎች ላይ በመመስረት የዳያስፖራውን ማህበረ-ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተሳትፎ የሚያሳድጉ ስራዎችን ለማከናወን ዝግጁ ነው ማታቸውን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት መረጃ ያመላክታል፡፡

በተለይም ዳያስፖራው በሀገር ውስጥ ያሉ የተሳትፎ ዕድሎችን የሚረዳባቸው ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን ለማመቻቸት ዝግጁ ነን ብለዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.