Fana: At a Speed of Life!

የሰላም ስምምነቱ በታቀደለት መንገድ እንዲፈጸም መንግሥት እየሠራ ነው- የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

በደቡብ አፍሪካ የተፈረመው የሰላም ስምምነት በታቀደለት መንገድ እንዲሄድ ለማድረግ የኢትዮጵያ መንግሥት እየሠራ ነው።

በዚህም መሠረት በመከላከያ ሥር ወዳለው አብዛኛውየትግራይ አካባቢ እርዳታ እንዲደርስ እየተደረገ ነው።

ወደተለቀቁት አካባቢዎች መሠረታዊ አገልግሎቶች ቀስ በቀስ እየተጀመሩ ነው።

በሌሎች አካባቢዎች አገልግሎቶችን ለማስጀመር እንዲቻል በታጣቂዎች የወደሙ መሠረተ ልማቶችን ለመጠገን ምቹ ሁኔታ እየተፈጠረ ነው።

ከዚሁ ጎን ለጎን በሰላም ስምምነቱ መሠረት የሕወሓት ታጣቂዎች ትጥቅ የሚፈቱበት ዝርዝር ዕቅድ ላይ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አዛዥና የሕወሓት ታጣቂዎች አዛዥ በናይሮቢመክረዋል።

በሰላም ስምምነቱ በተያዘው የጊዜ ገደብ ትጥቅ የሚፈታበትንና መከላከያ ወደ መቀሌ የሚገባበትን ዕቅድ ላይም ተስማምተዋል።

ዕቅዱም በቀጣይ ተግባራዊ ይደረጋል።

ለዕቅዱተግባራዊነት የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ በስምምነቱ መሠረት የሚጠበቅባቸውን ሊወጡ እንደሚገባ መንግሥት ያሳስባል።

ሕዳር 3 ቀን 2015 ዓ.ም

አዲስ አበባ

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.