Fana: At a Speed of Life!

ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ጋር ተወያዩ

አዲ አበባ፣ ሕዳር 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ኢቶ ታካኮ ጋር ተወያይዋል፡፡

በውይይታቸው ላይ ርዕሰ መስተዳድሩ የጃፓን ሕዝብ እና መንግሥት ለአማራ ክልል ልማት እያደረጉት ያለውን ድጋፍ አድንቀዋል፡፡

አምባሳደር ኢቶ ታካኮ በበኩላቸው÷ በሣይንስ እና ቴክኖሎጂ የሰለጠነ ብቁ የሰው ኃይል ለማፍራት ላለፉት ሰባት ዓመታት ከባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ጋር በትብብር እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የጃፓን ዩኒቨርሲቲዎች ከባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ጋር በትብብር በመስራት በትምህርት ዘርፍ የቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ነው ማለታቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡

በተጨማሪም የጃፓን መንግሥት ባሕር ዳር ከተማን ጨምሮ በአማራ ክልል በግብርና፣ በንፁህ መጠጥ ውሃ እና በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ላይ እየሠራ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

አምባሳደር ኢቶ ታካኮ በባሕዳር ከተማ አስተዳደር በሚገኙት ሰባታሚት የመጀመሪያ ደረጃ ሙሉ ሳይክልና ዘንዘልማ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሙከራ የምገባ መርሐ ግብር አስጀምረዋል፡፡

መርሐ ግብሩ ለቀጣይ አምስት ወራት ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን÷ ለዚህም በጃፓን መንግሥት የሚሸፈን ከ4 ነጥብ 1 ሚሊየን ዶላር በላይ በጀት ተመድቦለታል፡፡

የሙከራ ምገባ መርሐ ግብሩ ለሚቀጥሉት አምስት ወራት ታይቶ በኢትዮጵያ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች እንደሚተገበር ተመላክቷል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.