Fana: At a Speed of Life!

መንግሥት በኢስታንቡል ከተማ በደረሰው ጥቃት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ መንግሥት በትናንትናው ዕለት በቱርክ ኢስታንቡል ኢስቲካል ጎዳና ላይ በተፈጸመው የሽብር ጥቃት በደረሰው ጉዳት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ገለጸ፡፡
በጥቃቱ ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖች መጽናናትን ተመኝቷል፡፡
በተፈጸመው የሽብር ጥቃት የአካል ጉዳት ለደረሰባቸውም እንዲያገግሙ ተመኝቷል፡፡
የኢፌዲሪ መንግሥት በተፈጸመው ጥቃት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ገልጾ÷ ከቱርክ መንግሥት እና ሕዝብ ጎን መቆሙን አስታውቋል፡፡
በትናንትናው ዕለት በኢስታንቡል ኢስቲካል ጎዳና በተፈጸመ የሽብር ጥቃት÷ የሰው ሕይወት ማለፉ እና የአካል ጉዳትን ጨምሮ በንብረት ላይ ውድመት መድረሱ ይታወሳል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.