Fana: At a Speed of Life!

የተለያዩ ድርጅቶች የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚውል የገንዘብ ድጋፍ እያደረጉ ነው

አዲስ አበባ ፣መጋቢት 17፣2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ ድርጅቶች እና ግለሰቦች የኮሮና ቫይረ ስርጭትን ለመከላከል የሚውል የገንዘብ ድጋፍ እያደረጉ ነው።

በአሁኑ ወቅት የዓለም ስጋት የሆነውን የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ለመግታት የሚውል ገንዘብ ለማሰባሰብ ድርቶች እና ግለሰቦች ድጋፋ እንዲያደርጉ ጥሪ መቅረቡ ይታወቃል።

ይህን  ተከትሎም በዛሬው ዕለት የተለያዩ  ድርጅቶች እና ግለሰቦች በሀገሪቱ የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል የሚውል የተለያየ መጠን ያለው ገንዘብ ለጤና ሚኒስቴር አስረክበዋል።

በዚህ መሰረትም ፦

  • ብርሃን ኢንተርናሽናል ባንክ አክሲዮን ማህበር -5 ሚሊየን ብር
  • አንበሳ ጫማ ፋባሪካ እና ንፋስ ስልክ ቀለም- 5 ሚሊየን ብር
  • ዋሪት ሙሉጥላ ኢንተርናሽናል ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ-1 ሚሊየን ብር
  • የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን -1 ሚሊየን ብር
  • የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አትሌት ደራርቱ ቱሉ (በግል)-200 ሺህ ብር ድጋፍ አድርገዋል።

በድጋፍ ርክክብ ስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ፥ ተቋማቱ በሀገሪቱ የኮሮና ቫይረስ ስረጭትን ለመከላከል ላደረጉት የገንዘብ ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።

የተቋማቱ  ተወካዮች በበኩላቸው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ለመከላከል ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ  እንዲያደርግ አሳስበዋል።

በዙፋን ካሳሁን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.