Fana: At a Speed of Life!

በሪል እስቴቶች የሚገነቡ ቤቶች ከዝቅተኛ እስከ ከፍተኛ ገቢ ያላቸውን ዜጎች ታሳቢ ማድረግ አለባቸው- የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሪል እስቴቶች የሚገነቡ ቤቶች ከፍተኛ ገቢ ያላቸውን ብቻ ሳይሆን መካከለኛና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች ታሳቢ ያደረጉ መሆን እንዳለባቸው ተገለጸ፡፡

የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር በሀገሪቱ ካሉ የሪል እስቴት አልሚዎች ጋር ዘርፉን በሚመለከቱ አጠቃላይ ጉዳዮች እና በቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ መክሯል፡፡

የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ወንድሙ ሴታ እንደተናገሩት÷ ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት አስርት ዓመታት በከተሜነት ምጣኔዋ ካደጉት ሀገራት መካከል እንድትመደብ የቤት አቅርቦት ወሳኝ ነው፡፡

የመኖሪያ ቤት ችግርን ለመቅረፍ÷ ከተለመደው የአሠራር ሥርዓት መውጣት፣ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን መፍጠር፣ የግንባታ ግብዓቶችን በሀገር ውስጥ ባሉ ቁሶች መጠቀም እና ከጥራት፣ በጀት እና ከጊዜ ጋር ተያይዞ የሚስተዋሉ ችግሮችን መቅረፍ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

የሪል እስቴት ዘርፉ ከፍተኛ ገቢ ካላቸው ነዋሪዎች አልፎ መካከለኛ እና ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ተደራሽ እንዲሆን መሥራት ይገባል ማለታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

በሚኒስቴሩ የቤቶችና ከተማ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ሄለን ደበበ በበኩላቸው÷ የመኖሪያ ቤት ችግርን ለመቅረፍ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ተግባራዊ በማድረግ በተደራጀና በተቀናጀ መልኩ ተናቦ መሥራት እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.