Fana: At a Speed of Life!

የሊጉ 8ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ከፊታችን ረቡዕ ጀምሮ መካሄድ ይጀምራሉ

አዲስ አበባ፣ህዳር 5፣2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በስታዲየም ብልሽት ተራዝመው የቆዩት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 8ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ከፊታችን ረቡዕ ጀምሮ መካሄድ ይጀምራሉ፡፡
 
በዚህም መሰረት ረቡዕ ቀን 10 ሰዓት ሀድያ ሆሰዕና ከሀዋሳ ከነማ ጨዋታቸውን ሲያደርጉ÷ ምሽት 1 ሰዓት ደግሞ ሲዳማ ቡና ከኢትዮጵያ ቡና ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡
 
መርሐ ግብሩ ሀሙስ ቀጥሎ ሲካሄድ አዳማ ከተማ ከወላይታ እንዲሁም ቅዱስ ጊዮርስ ከመቻል ጨዋታቸውን የሚያከነውኑ መሆኑን ሊግ ኩባንያው አስታውቋል፡፡
 
የሊጉ 8ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በድሬዳዋ ስታዲየም ብልሽት ምክንያት ለተወሰኑ ቀናቶች መራዘማቸው የሚታወስ ነው፡፡
 
ፕሪሚየርሊጉን ኢትዮጵያ መድን በ15 ነጥብ ሲመራ ቅዱስ ጊዮርጊስ በ14 ነጥብ ይከተላል፡፡
 
የኮከብ ጎል አግቢነቱን ደረጃ ደግሞ የቅዱስ ጊዮርጊሱ አጥቂ እስማኤል ኦሮ አጉሮ በ9 ግቦች ሲመራ÷የወልቂጤ ከነማው አጥቂ ጌታነህ ከበደ በ5 ግቦች 2ኛ እንዲሁም ሙጅብ ቃሲም ከሃዋሳ ከተማ 3ኛ ደረጃን ይዟል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.