Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ማክሮ ኢኮኖሚ ዓለም አቀፋዊውን ጫና ተቋቁሞ መሻገር ችሏል – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 6 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ማክሮ ኢኮኖሚ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያጋጠመውን ጫና ተቋቁሞ መሻገር መቻሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ ሠጥተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማብራሪያቸው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላለፉት ዓመታት ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ ፈተናዎች ገጥመውት እንደነበር አንስተዋል፡፡

በተለይም በሀገራችን በሰሜኑ ክፍል ያጋጠመው ጦርነት፣ በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል የተከሰተው ጦርነት፣ ድርቅ ፣ የኮሮና ቫይረስ እና የመሳሰሉት ዋና ዋናዎቹ መሆናቸውንም ዘርዝረዋል፡፡

ነገር ግን የኮሮና ቫይረስ በመቀስቀሱ የዓለማችን በርካታ ሀገራት ዜጎቻቸው በቤታቸው እንዲሆኑ በገደቡበት ወቅት እኛ ግን በመሥራታችን ምንም እንኳን ጫናው ባይቀርልንም የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ግን ሳይሰበር ዓለም አቀፋዊ ጫናውን ማለፍ ችሏል ነው ያሉት፡፡

አያይዘውም በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ወቅት በር ዘግተን ባለመቀመጣችን እና በመሥራታችን አሁን የምናወራለትን የእርሻ ምርት ማምረት ችለናልም ብለዋል።

መስራት በመቻሉም በ2014 በጀት ዓመት 6 ነጥብ 4 በመቶ ጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ዕድገት ማስመዝገብ መቻሉን አስረድተዋል።

በ2015 በጀት ዓመት ደግሞ 7 ነጥብ 5 በመቶ ጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ዕድገት ለማስመዝገብ ዕቅድ መያዙንም ጠቅሰዋል።

በዓለማየሁ ገረመው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.