Fana: At a Speed of Life!

መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ ኤምባሲዎች የወታደራዊ አታሼዎች ስለ ሰላም ስምምነቱ ማብራሪያ ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በፌደራል መንግስትና በህወሓት መካከል ስለተደረሰው የሰላም ስምምነት መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ ኤምባሲዎች የወታደራዊ አታሼዎች ማብራሪያ ተሰጠ።

ማብራሪያውን የሰጡት የመከላከያ የውጭ ግንኙነት እና ወታደራዊ ትብብር ዳይሬክተሩ ሜጀር ጄነራል ተሾመ ገመቹ ናቸው፡፡

ሜጀር ጄነራል ተሾመ ዛሬ ኢትዮጵያ በአዲስ የተስፋ ምዕራፍ ላይ ትገኛለች ብለዋል፡፡

የሰላም ስምምነቱ ግጭትን በዘላቂነት የማስቆም ስምምነት መሆኑንም ነው የገለጹት፡፡

የመከላከያ ሰራዊቱ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ማስከበሩን እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል፡፡

የሰብዓዊ ድጋፉም በትግራይ፣ አማራ እና አፋር ክልሎች በተቀላጠፈ መንገድ እንዲደርስ የሚደረገው ጥረት እንደሚጠናከር ነው የተናገሩት፡፡

ሰራዊቱ አሁን ላይ በትግራይ ክልል ገንዘብ በማሰባሰብ፣ የህክምና አገልግሎትን እየሰጠ ነው ብለዋል፡፡

ሜጀር ጄኔራሉ የተፈናቀሉ ዜጎችም ወደ መኖሪያ ቀያቸው እንዲመለሱ እየተሠራ ነውማለታቸውን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ኬንያ ላይ የተደረገውን ስምምነት በተመለከተም ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.