Fana: At a Speed of Life!

17ኛው የቡድን 20 አባል ሀገራት ጉባዔ በኢንዶኔዢያ ዛሬ ይጠናቀቃል

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 7 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 17ኛው የቡድን 20 አባል ሀገራት ጉባዔ በኢንዶኔዢያ ባሊ እየተካሄ ነው።

በዛሬው ዕለት በጉባዔው የሚነሱ የውይይት ነጥቦች በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ላይ ያተኩራሉ ተብሏል፡፡

“በአንድነት እናገግም፣ እንጠንክር” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ የሚገኘው የሀገራቱ ጉባዔ ዛሬ ይጠናቀቃል መባሉን የዘገበው ሲ ጂ ቲ ኤን ነው፡፡

ከጉባዔው በፊት የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ እና የአሜሪካው አቻቸው ጆ ባይደን ፊት ለፊት ተገናኝተው በወቅታዊ እና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.