Fana: At a Speed of Life!

ፖላንድን የመታው ሚሳኤል ከዩክሬን የተወነጨፈ ሳይሆን አልቀረም ተባለ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ፖላንድ በፀረ-አውሮፕላን ሚሳኤል መመታቷ ተነገረ፡፡

የፖላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ማቴዝ ሞራዊኪ ÷ ብሔራዊ የደኅንነት እና መከላከያ ሚኒስትሮቻቸውን አስቸኳይ ስብሰባ ጠርተዋል፡፡

ሩሲያ የተኮሰችባትን ሚሳኤል ለማክሸፍ ዩክሬን በወሰደችው አጸፋዊ ምላሽ ሚሳኤሉ አቅጣጫውን ስቶ ፖላንድን ሳይመታ እንዳልቀረም እየተነገረ ነው፡፡

ፖላንድ ጉዳዩ በሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) አንቀፅ 4 ላይ በሰፈረው ስምምነት መሠረት እንዲታይ አቤቱታ አቅርባለች።

በአንቀጹ መሠረት ሉዓላዊነቴ ተደፍሯል ማለቷን ዶቸቬሌ ዘግቧል፡፡

ኔቶ ፣ አሜሪካ ፣ የአውሮፓ ኅብረት እና ብሪታኒያ በጉዳዩ ላይ ትክክለኛው መረጃ ከመውጣቱ በፊት አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡

አሜሪካ ፣ ጀርመን እና ቱርክ ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተሉት እንደሆነ ከሚሰጧቸው አስተያየቶች የታወቀ ሲሆን ቻይና ግን ዝምታን መምረጧ ነው የተነገረው፡፡

በፍንዳታው የሁለት ሰዎች ሕይወት ማለፉ ታውቋል፡፡

ጥቃቱን ያደረሰችው ሩሲያ ብትሆን አንቀፅ 5 ላይ በተመለከተው የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት አባል ሀገራት ሥምምነት መሠረት ጥምር የጦር ጥቃትን የሚጨምር ከባድ መዘዝ እንደሚጠብቃት ዩራክቲቭ ፅፏል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.