Fana: At a Speed of Life!

በናይሮቢና በፕሪቶሪያ የሠላም ስምምነት ሰነዶች መካካል መሠረታዊ ልዩነት የለም – ዶክተር ለገሰ ቱሉ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በይዘት ደረጃ በናይሮቢና በፕሪቶሪያው የሠላም ስምምነት ሰነዶች መካካል መሠረታዊ ልዩነት እንደሌለ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ ገለጹ፡፡

ዶክተር ለገሰ ቱሉ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷ የፕርቶሪያው ሰነድ ወሳኝ፣ የማይከለስ፣ የማይበረዝና ለሌሎች መሠረት ሆኖ የሚያገለግል እናት ዶክመንት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የናይሮቢው ሰነድ ደግሞ የማስፈፀሚያ ዕቅድ መሆኑን ጠቁመው÷ ከአቋም አኳያም የተቀየረ ነገር አለመኖሩን አስገንዝበዋል፡፡

መከላከያ ሠራዊቱን ያጠቃና ለኅልውና አደጋ የዳረገው ኃይል ትጥቅ ከፈታ እና ተኀድሶ ከገባ÷ ድሮውንም ተገደው የገቡ ከመከላከያ ውጪ ያሉ ኃይሎች  እንደሚወጡ ጠቁመዋል፡፡

ይህም ተፈጻሚ እንደሚሆን ነው ዶክተር ለገሰ  ቱሉ የገለጹት፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.