Fana: At a Speed of Life!

በአሜሪካ የአጋማሽ ዘመን ምርጫ ሪፐብሊካኖች በኮንግረሱ አብላጫ ወንበር አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ የአጋማሽ ዘመን ምርጫ ሪፐብሊካኖች በተወካዮች ምክር ቤት አብላጫ ወንበር አሸንፈዋል።

በምርጫው ሪፐብሊካኖች እስካሁን የምክር ቤቱን መቀመጫ ለመቆጣጠር የሚያስፈልጋቸውን 218 ወንበሮች አግኝተዋል ነው የተባለው።

ሪፐብሊካኖች ተጠባቂውን የካሊፎርኒያ 27ኛ አውራጃ ምርጫ ማይክ ጋርሺያ ማሸነፋቸውን ተከትሎ አብዛኛውን የምክር ቤት መቀመጫ ማሸነፍ መቻላቸውን አረጋግጠዋል፡፡

በምርጫው በየግዛቶቹ የተሰጡ ድምፆች ተቆጥረው ያላለቁ ሲሆን ሪፐብሊካኖቹ ከ435ቱ መቀመጫዎች ከ218 እስከ 223 መቀመጫዎች እንደሚያሸንፉ ይጠበቃል ተብሏል፡፡
ውጤቱን ተከትሎም የዴሞክራቷን ተወካይና የምክር ቤቱ አፈ ጉባዔ ናንሲ ፔሎሲን ለመተካት ኬቨን ማካርቲ ዕጩ መሆናቸውን ቢ ቢ ሲ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.